ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ኬንያ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳለጥ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ትናንት የተጀመረው የኢትዮ-ኬንያ የድንበር ላይ ንግድ ድርድር መቋጨቱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለት ከኬንያ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሊ ኪንያንጁ ጋር የትግበራ ስምምነት መፈራረማቸውን አመላክተዋል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት በሚያሳልጥ አግባብ የተፈረመ መሆኑን የገለጹት ካሳሁን (ዶ/ር)÷ በድንበር አካባቢ የሚገኙ ህዝቦች የመሰረታዊ የዕለት ፍጆታ ያለምንም የአቅርቦት ችግር እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነም ጠቁመዋል።