Fana: At a Speed of Life!

የሚፈጠሩ እድሎች እና ስጋቶችን በመመዘን የሀገሪቱን ጥቅም ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ሀገራዊ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አድርገዋል።

በመድረኩ ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍፁም አረጋ÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የነበረው የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ምርታማነትን እና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እንዳስቻለ ገልጸዋል።

በዲፕሎማሲ መስክ የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረኮች ኢትዮጵያ ተሳትፎዋን ማሳደግ እና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ ያስቻሉ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተዋል።

በዘጠኝ ወራት በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተላከ ገንዘብ ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ገንዘብ ወደ ሀገር ውስጥ መላኩና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር 12 በመቶ እድገት እንዳለው ተጠቅሷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)÷ ባለፉት ሰባት ዓመታት የተተገበሩ ሁለንተናዊ የሪፎርም ስራዎች የኢትዮጵያን የእድገት ማነቆዎች ለመፍታት እና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያስቻሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመጪው ጊዜ የሚፈጠሩ እድል እና ስጋቶችን በጥልቀት በመመዘን የሀገሪቱን ጥቅም ለማሳደግ መስራት እንደሚገባ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.