Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየው የቀድሞ ታጣቂዎች የተሃድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ዳግም ተጀምሯል።

የአፍሪካ ሕብረትና የዓለም አቀፍ ተቋማት ታዛቢዎችና ተወካዮች ለቀድሞ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች የሚሰጠውን የተሃድሶና መልሶ ማቋቋም የስልጠና ሒደት ተመልክተዋል።

በምልከታው የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን፣ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሌ/ጄ ፍስሀ ኪዳኑ፣ በአፍሪካ ሕብረት የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የቁጥጥር፣ ማረጋገጥና ማስከበር ተልዕኮ ልዑክ ኃላፊ ሜ/ጄ ሳማድ አላዴ፣ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የአጋር የልማት ድርጅቶችና የሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለቀድሞ ታጣቂዎች የሚሰጠው የተሃድሶና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የቀድሞ ታጣቂዎችን የማረጋገጥ፥ ዲሞቢላይዝ የማድረግ፣ የመመዝገብና የተሃድሶ ስልጠና በመስጠት ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ዳግም ዛሬ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ መጀመሩን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክልሉ የቀድሞ ታጣቂዎችን የዲሞብላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ስልጠና ሕዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም መጀመሩ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.