Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት መጎልበት የቴክኖሎጂው ዘርፍ ጉልህ ሚና አለው – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት መጎልበት የቴክኖሎጂው ዘርፍ የላቀ ሚና አለው ሲሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች የ2017 ዓ.ም የ9 ወር የእቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሂደዋል።

በመድረኩ የተገኙት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ÷የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ይዞ በመጣው ለውጥ ውስጥ ሁሉም ዜጋ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መሳተፉን ጠቁመው፤የተሰሩ ሥራዎችን መረዳት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ስንሰራ በመካከላችን ያሉ አላስፈላጊ ግንቦችን በማፍረስ በትብብር የምንሰራበትን ሁኔታ መፍጠር ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ የመሰረተ ልማት፣ የሰው ሃይል ግንባታ፣ የፖሊሲና ስትራቴጂ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማጎልበት ውስብስብ የፋይናን ሥርዓቱን ለማቃለልና የሥራ እድል ለመፍጠር የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከፍተኛ አስተዋኦ እንዳስገኘ ተናግረዋል።

በቴክኖሎጂ የዘመነችና ለሌሎች ሀገራት አርአያ የሆነች ኢትዮጵያን ለመገንባት በትኩረት መስራት ይገባል ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.