Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ባንክ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ያካሄደው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ውጤት ይፋ ሆኗል።

በጨረታ ሒደቱ 26 ባንኮች የተሳተፉ ሲሆን÷በዚህም የምንዛሪ ጨረታ ዋጋ አንድ የአሜሪካን ዶላር ዋጋ በአማካኝ 131 ነጥብ 4961 ብር ሆኖ መመዝገቡ ተገልጿል፡፡

የውጭ ምንዛሪ የገበያ ሁኔታን በቅርበት በመከታተል እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሪ ሽያጮችን እንደሚያካሂድ የባንኩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቀጣዩ የውጪ ምንዛሪ ጨረታም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.