Fana: At a Speed of Life!

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ትልቅ ዕድል የከፈተ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ትልቅ ዕድል የከፈተ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ተገኝተው የኮሚሽኑን የስራ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ምህዳር በእጅጉ ያሻሻሉ የሪፎርም ተግባራት እንዳከናወነ ማየታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ እና ዘመናዊ የዲጂታል አሰራሮችን የተከተለ የደንበኞች አገልግሎት አሰራርን ተግባራዊ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለዘርፉ ትልቅ ዕድል የከፈተ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ የተገኘው ስኬት ይህንኑ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በቀጣይ ኮሚሽኑ የጀመረውን አበረታች እና ከኢኮኖሚ ዕቅዶቻችን ጋር የተጣጣመ ዒላማ ተኮር የኢንቨስትመንት አማራጮች በማስተዋወቅ የኢንቨስትመንት ፍሰት ማሳደግ ላይ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠናልም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.