Fana: At a Speed of Life!

ኢግልድ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር ዘይትን ጨምሮ ሌሎች የበዓል ፍጆታዎችን ለገበያ እያቀረበ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) ለትንሳዔ በዓል መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ እያቀረበ መሆኑን አስታውቋል፡

የኢግልድ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ሲሳይ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፥ ተቋሙ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የዋጋ ንረትን በማረጋጋት ረገድ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

በዚህ መሰረትም ለትንሳዔ በዓል የተለያዩ ምርቶችን ለገበያ ለማቅረብ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ለበዓሉ 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ሊትር የፈሳሽና ፖልም ዘይት አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ለገበያ ማቅረቡን ገልጸዋል።

የአምስት ሊትር ፈሳሽ ዘይት ዋጋ 1 ሺህ 250 ብር መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፥ አንድ ሰው መግዛት የሚችለው አንድ ባለ 5 ሊትር ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በርካታ መጠን ያለው ባለ 50፣ 25፣ 10 እና 5 ኪሎ ስንዴ ዱቄት ለተጠቃሚዎች መቅረቡን ነው ያስረዱት።

በሌላ በኩል ኢግልድ ፓስታና ሌሎች የትንሳዔ በዓል መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመሸጫ ሱቆቹ እያቀረበ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ስለሆነም ሕብረተሰቡ እስከ ፊታችን ቅዳሜ ድረስ ወደ መሸጫ ሱቆች በመሄድ ምርቶችን እንዲሸምት ጠቁመዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.