Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው 4ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በሦስት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

አጀንዳዎቹም ፦
1ኛ. ተቋርጦ የነበረው የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።

2ኛ. የብርሃን ዓይነ ስውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ትምህርት ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማው ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበውን ደንብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ ማጽደቁን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.