ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሃኖይ የሚገኘውን የ1ኛና 2ኛ ደረጃ የዓይነስውራን ት/ቤት ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሃኖይ የሚገኘውን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የዓይነስውራን ትምህርት ቤት ጎብኝተዋል፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ዛሬ የቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ቀዳማዊት እመቤት ማዳም ነኹ በሃኖይ የሚገኘውን የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ የአይነስውራን ት/ቤት አስጎብኝተውኛል ብለዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኘው እና በተለያዩ ክልሎች እየተሰሩ ላሉ አዳዲስ የዓይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚሆኑ ተሞክሮዎች ማግኘታቸውን ገልጸዋል።