Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው – አቶ አሻድሊ ሀሰን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ፡፡

በአሶሳ ከተማ የሚገኘውን ሞዴል የወጣቶች መዝናኛ ማዕከልን የጎበኙት ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ÷ መንግስት ለወጣቶች ስብዕና ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ያለውን አቅም ለሀገር ግንባታ እንዲያውል ለማስቻል ምቹ የመዝናኛ ማዕከላትን መገንባት እና በሥነ ምግባር የዳበረ ትውልድ መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙ የመዝናኛ ማዕከላትን በማጠናቀቅ ለወጣቶች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እየተደረገ ያለው ጥረት የሁሉም ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በአሶሳ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን ጉዳት የደረሰባቸው ሴቶች ማገገሚያና የስልጠና ማዕከል የተመለከቱ ሲሆን÷ ግንባታው በጥራት፣ በፍጥነትና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ የቅርብ ክትትል ይደረጋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.