ነገሌ አርሲ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አደገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ እየተሳተፈ የሚገኘው ነገሌ አርሲ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።
ዛሬ የምድብ 21ኛ ጨዋታውን ያደረገው ነገሌ አርሲ ስልጤ ወራቤን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ውጤቱን ተከትሎም ክለቡ አንድ ጨዋታ እየቀረው በ46 ነጥብ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል፡፡