Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በሰው እና በሮቦቶች መካከል የመጀመሪያውን የግማሽ ማራቶን ውድድር አካሄደች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቻይና በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ሰዎች እና ሮቦቶች የተሳተፉበት የግማሽ ማራቶን ውድድር በቤጂንግ አካሂዳለች፡፡

21 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው የግማሽ ማራቶን ውድድር ከ9 ሺህ በላይ ጀማሪ አትሌቶች እና 20 ከሚጠጉ የሮቦቲክስ ኩባንያዎች የተውጣጡ ሮቦቶች ተሳትፈውበታል፡፡

በውድድሩ ላይ የተሳተፉ የሰው ቅርጽ ያላቸው ሮቦቶች መራመድ አልያም መሮጥ ብቻ የሚችሉ እንጂ ጎማ ያልተገጠመላቸው እንደነበሩም ተገልጿል፡፡

ውድድሩን ከቤጂንግ ሰው መሳይ ሮቦቶች ፈጠራ ማእከል የሆነችው ቲያንጎንግ አልትራ የተባለችው ሮቦት 2 ሰአት ከ40 ደቂቃ በሆነ ሰአት አሸናፊ ሆናለች።

ባለፉት ዓመታት በቻይና ሮቦቶች በማራቶን ላይ ሲሳተፉ ቢታዩም ከሰዎች ጋር ሲወዳደሩ ግን ይህ የመጀመሪያው መሆኑን የቻይና ዴይሊ ዘገባ ያመላክታል።

በውድድሩ ላይ አስደናቂ ብቃት ያላቸው ሮቦች የታዩ ሲሆን በሰዎች እና በማሽኖች መካከል እያደገ የመጣውን ውህደት አጉልቶ አሳይቷልም ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.