Fana: At a Speed of Life!

በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ ለቆዳና ሌጦ ጥራት ሲባል ሊወሰዱ የሚባቸው ጥንቃቄዎች…

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቆዳና ሌጦ ምርት ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን ከፍተኛ ጥቅም በመገንዘብ ባለድርሻ አካላት በእርድ ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ፡፡

በእርድና ከእርድ በኋላም ቀጥለው የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች መተግበር እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አሳውቋል፡፡

ለእርድ የሚቀርበውን እንስሳ በዱላ አለመምታት፤

እንስሳው የሚታረድበት ቦታ ንፁህ ማድረግና ለእርድ ሲጣል ከመሬት ጋር አለማጋጨት፤

እንስሳው ሲታረድ ደሙ ተሟጦ እንዲወጣ ማድረግ፤

ቆዳው ሲገፈፍ የተፈጥሮ መስመርን ወይም ቅርፅን ተከትሎ መሰንዘር፤

ቆዳው ሲገፈፍ በቢለዋ እንዳይበሳ መጠንቀቅ፤

ቆዳው ሲሰበሰብ መሬት ላይ አለመጎተት እና አለማቆሸሽ፤

ቆዳው ሲሰበሰብ እንዳይበሰብስ ጥንቃቄ ማድረግና መሬት ላይ አለማድረቅ፤

እርድ ሲከናወን ለቆዳና ሌጦ ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች በመተግበር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ለመጨመር ሁሉም አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ሚኒስተሬሩ ጥሪ አቀርቧል፡፡

በእርድ ወቅትና ከእርድ በኋላ ለቆዳና ሌጦ አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት በጥራት በማዘጋጀት ለተረካቢዎች መሸጥ፤ ተረካቢዎችም በጥራት በማከማቸት ለኢንዱስትሪዎች ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.