Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 25ኛውን ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ስራ አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 25ኛውን ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ጉራራ ቅርንጫፍ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ከንቲባዋ በአዲሱ ማዕከል የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግርች ለተጋለጡ ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚህ ወቅት÷ ከተማ አስተዳደሩ ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር የምገባ ማዕከላትን በማስፋፋት በቀን አንድ ጊዜ መብላት የማይችሉ ወገኖችን እየመገበ መሆኑን ተናግረዋል።

25ኛውን የምገባ ማዕከል በአያት አክሲዮን ማህበር ድጋፍ መገንባቱን ጠቅሰው፥ ድርጅቱ በማዕከሉ አቅመ ደካማ ወገኖችን የሚመግብ በመሆኑም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መስጠት አያጎድልም፤ መለገስም በረከት ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ በቀጣይም ባለሀብቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ማዕከሉ በቀጣይ በየቀኑ ከ300 እስከ 500 በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት የማይችሉ ወገኖችን እንደሚመግብ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.