Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከጤና ባለሙያዎችና ታካሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን አከበሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት የጤና አገልግሎት እየሰጡ ካሉ ባለሙያዎች እና ታካሚዎች ጋር የትንሳዔ በዓልን አክብረዋል።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ÷ ታካሚዎችን በበዓላት ወቅት ማከም ትልቅ ደስታ እንደሚፈጥር ጠቅሰው፣ የጤና ሙያ ራስን ሰጥቶ ህበረተሰቡን ማገልገል እንደሆነ ተናግረዋል።

ለሕብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ከማሻሻል ጎን ለጎን የጤና ባለሙያውን ሕይወት ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀየር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል::

በተመሳሳይ ሚኒስትሯ ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘዉ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ተገኝተው ማዕድ በማጋራት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በወቅቱም ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 4 ሚሊየን ብር ዋጋ ያለው ዘመናዊ የአልትራሳውንድ ማሽን ተበርክቷል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አረጋዊያንን ከወደቁበት አንስቶ እየደገፈ ራሳቸዉን ከመቻል አልፈው ለሌሎች እንዲተርፉ በማድረግ አርዓያነት ያለው ስራ እያከነወነ እንደሚገኝ ዶ/ር መቅደስ መግለጻቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.