የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሌጎስ የሚያርገውን ሳምንታዊ በረራ በእጥፍ አሳደገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄርያ ሌጎስ ከተማ እያደረገ ያለውን 7 ሳምንታዊ በረራ ከሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ 14 ሳምንታዊ በረራ አሳደገ፡፡
ይህም ለደንበኞቹ ይበልጥ ምቹ የበረራ አማራጭ መስጠት የሚያስችል መሆኑን አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡