Fana: At a Speed of Life!

3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 285 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ተመላሾቹ 2 ሺህ 747 ወንዶች፣ 508 ሴቶች እና 30 ጨቅላ ሕጻናት ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥም 159 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ እስካሁን 18 ሺህ 969 ኢትዮጵያውያንን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.