በ311 ሚሊየን ብር የተገነባው የሆራአዘብ ከተማና አካባቢ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ311 ሚሊየን ብር የተገነባው የሆራአዘብ ከተማና አካባቢ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር ) በጋራ መርቀው ከፍተዋል።
በኩርሙክ ወረዳ የሆራአዘብ ከተማ እና አካባቢ ቀበሌዎች የንጹህ መጠጥ ውሃና ሥነ-ንፅህና ፕሮጀክት ከ15 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡