የዞን አምስት ወርልድ ቴኳንዶ ውድድር ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የተሳተፉበት የዞን አምስት ወርልድ ቴኳንዶ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።
የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ያዘጋጀው ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እየተካሄደ ነው።
ውድድሩ በጁንየር፣ በካዴትና በሲንየር ተለይቶ በሶስት ምድቦች እየተካሄደ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።