ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በልምምድ ወቅት ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በለንደን ማራቶን እንደማይሳተፍ አስታውቋል፡፡
በሩጫ ሕይወቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደግፉትና ለሚያበረታቱት አድናቂዎች ምስጋናውን ያቀረበው አትሌት ቀነኒሳ÷ አሁን ላይ ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ትኩረቱን እንደሚያደርግ ገልጿል።
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት÷ ከፊታችን እሁድ በሚካሄደው ውድድር ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶችም መልካም ዕድል ተመኝቷል።