Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከካሜሩን ለሚጓዙ ሃጃጆች የበረራ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካሜሩን ለሚጓዙ ሃጃጆች እንዲሁም ወደ ያውንዴ እና ዱዋላ የሚያደርገውን መደበኛ የበረራ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የካሜሩን የግዛት አስተዳደር ሚኒስትር እና የሃጅ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ፖል አታንጋ ንጂ ከልዑካቸው ጋር በመሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አገልግሎትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም÷ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡድን ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና ከሌሎች የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ጋር ፍሪያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካሜሩን ለሚጓዙ ሃጃጆች እንዲሁም ወደ ያውንዴ እና ዱዋላ የሚያደርገውን መደበኛ የበረራ አገልግሎት ለማከናወን ቁርጠኛ እንደሆነ መግለጹን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.