Fana: At a Speed of Life!

ርዕስ መሥተዳድር ሙስጠፌ 4ኛውን ክልላዊ የሥራ ፈጠራ ውድድር አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ 4ኛውን ክልላዊ የሥራ ፈጠራ ውድድር መርሐ-ግብር አስጀምረዋል፡፡

በክልሉ በቴክኒክ ሙያ ኮሌጆች መምህራን እና ተማሪዎች የሚዘጋጁ የፈጠራ ሥራዎች የማኅበረሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የሚያቃልሉ ሊሆኑ እንደሚገባም አቶ ሙስጠፌ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል፡፡

ለውድድሩ የሚቀርቡ የፈጠራ ሥራዎች የማኅበረሰቡን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉና ሊበረታቱ የሚገባቸው ናቸው ብለዋል፡፡

መንግሥት የሚያደርገው ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

በውድድሩ ላይ በ12 የቴክኒክ ሙያ እንዲሁም በ34 የትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች መምህራን፣ በ59 ተማሪዎች እና 2 የግል ድርጅቶች ተዘጋጅተው ለዕይታ ከቀረቡ የፈጠራ ሥራዎች መካከል፤ የሰብል ምርት መሰብሰቢያ ማሽኖች፣ የዶሮ መፈልፈያ፣ የእንስሳት መኖ ማዘጋጃና ለቤት ግንባታ የሚውሉ ይገኙበታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.