ካዛንቺስ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ሆናለች – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ካዛንቺስ ዛሬ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ሆናለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ካዛንቺስ የድካማችን ትዕምርት፤ የስንፍናችን ሰንደቅ ነበረች፤ ዛሬ የኢትዮጵያ ትንሣኤ ምልክት ሆናለች ብለዋል።
ካዛንቺስ ከተማ እንዴት መልሶ እንደሚገነባ ኅያው ትምህርት ቤት ናት ያሉት አቶ ተመስገን፤ ንግድ፣ አገልግሎት፣ መዝናኛ፣ መሠረተ ልማት እንዴት በብልጽግና ሐሳብ እንደሚገነቡ አጉልታ ታሳያለች፤ ጮኻ ትናገራለች ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ካዛንቺስ ለሕጻናት፣ ለወጣቶች፣ ለጎልማሶች፣ ለአረጋውያን የሚሆን ከተማ ምን እንደሚመስል በኤግዚቢሽንነት ታስረዳለች ነው ያሉት፡፡
ካዛንቺስ እንደገና በልዩ ሁኔታ ስለተወለድሽ እንኳን ደስ አለሽ፤ አንቺን የፈጠረ ሐሳብ፣ የገነቡ እጆች አስደናቂ ናቸው ሲሉም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡