Fana: At a Speed of Life!

በትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ኔጌሌ አርሲ ወረዳ ራፉ ሃርጊሳ ቀበሌ በደረሳ የትራፊክ አደጋ የ16 ሰዎች ሕይዎት ሲያልፍ በ22 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል አካል ጉዳት ደረሰ፡፡

አደጋው የደረሰው፤ ከሻሸመኔ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ባለ ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጋር በማጋጨቱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አደጋውን ተከትሎም ከሟቾች በተጫመሪ በ16 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ6 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የኔጌሌ አርሲ ከተማ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.