Fana: At a Speed of Life!

ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም የሚገኘውን ባዮ ማስ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች በመጠቀም የውጭ ምንዛሪ ብክነትን ማዳን መቻሉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም የሚገኘውን ባዮ ማስ ለሲሚንቶ ፋብሪካዎች በመጠቀም የውጭ ምንዛሪ ብክነትን ማዳን ተችሏል ሲል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአፋርና በሶማሌ ክልሎች በስፋት እየተዛመተ ያለውን የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረምን ለሀይል አማራጭነት በመጠቀም ከውጭ የሚገባን የምርት ግብዓት መተካት መቻሉን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከአረሙ የሚገኘውን ባዮ ማስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በግብዓትነት መጠቀም ስለጀመሩ፤ ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል በመቀነስ 2 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ብክነትን ማዳን እንደተቻለ አብራርተዋል ፡፡

ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም የሚመረተው ባዮ ማስ በአሁኑ ሠዓት የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የሚጠቀሙትን የድንጋይ ከሰል እስከ 20 በመቶ እየተካ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.