Fana: At a Speed of Life!

የህዝባችንን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ ያስፈልጋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ ክልል መንግስት እና የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ተጠናቋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን በስራ ላይ በማዋል፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል እና የጋራ ሃይልን በማሰባሰብ ለልማት በማዋል ስኬታማ ስራ መሰራቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።

የህዝቡ የመልማት ፍላጎት እና ጥያቄ ከፍተኛ በመሆኑ በአፈጻጸም በተገኘው ስኬት ሳንኩራራ በቀጣይ ለተሻለ ስራ መዘጋጀት ይኖርብናል ሲሉም ተናግረዋል።

የህዝባችንን ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ የግድ በመሆኑ በቀሪ የበጀት አመቱ ወራት በእቅድ መስራት ይኖርብናል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።

በዚሁ ጊዜያት የተያዙ ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ እና ህዝባዊ እርካታን ለማሳደግ መሰራት እንዳለበት በማጠቃለያ መድረኩ ላይ አንስተዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቀጣይ በጀት አመት ከዚህኛው በጀት አመት የተሻለ የስራ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ከፍተኛ ዝግጅት እንዲደረግ አሳስበዋል።

የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ከፍያለው ተፈራ በበኩላቸው የዘጠኝ ወራቱ አፈጻጸም የተሳካ እንደነበር አንስተው ለቀጣይ ስራ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንዖት ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.