Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል የቡና ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል የቡና ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሸበዲኖ ወረዳ ፉራ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።

የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት÷ በክልሉ ከ29 ሚሊየን በላይ የተሻሻለ የቡና ችግኝ ለመትከል ታቅዷል።

ለዚህም ሙሉ ፓኬጅ በመጠቀም ወደ ተከላ የተገባው መርሐ ግብሩ በክልሉ የቡና ምርትና ምርታማነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አመላክተዋል።

በባህር ዛፍ የተያዘውን ሰፊ መሬት ነጻ በማድረግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የቡና ልማት ላይ እንዲውል እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

በዚህም በክልሉ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ችግኝ ተከላ እንደሚካሄድ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.