የኢትዮጵያ አቪዬሽን ፎረም እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት ተደራሽነት ማስፋት ላይ ያተኮረ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በፎረሙ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰውና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በመድረኩ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከዓለም ጋር ማስተሳሰር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአህጉር አቀፍ ደረጃ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ነው የተጠቀሰው፡፡
ፎረሙ በአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን መፍታት በሚቻልባቸው ሁኔታቸው ላይ እንደሚያተኩርም ተመላክቷል፡፡
በአመለወርቅ መኳንንት