Fana: At a Speed of Life!

ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ ከሌስተር ሲቲ ጋር የሚለያየው ጄሚ ቫርዲ…

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ጄሚ ቫርዲ ከ13 ዓመታት ቆይታ በኋላ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከሌስተር ሲቲ ጋር እንደሚለያይ ክለቡ አስታውቋል፡፡

ሌስተር ሲቲ በፈረንጆቹ 2015/16 የውድድር ዓመት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ የቫርዲ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ጄሚ ቫርዲ ሌስተር ሲቲን ከሻምፒዮን ሺፕ ጀምሮ እስከ ፕሪሚየር ሊግ ያገለገለ ተጨዋች ሲሆን÷ በክለቡ 496 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡

የ38 ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች 198 ጎሎችን በማስቆጠር የሌስተር ሲቲ የምን ጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው፡፡

በሌስተር ሲቲ በነበረው ቆይታም የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ የኤፍ ኤ ካፕ እና የኮሙኒቲ ሽልድ ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል፡፡

ሌስተር ሲቲ በዚህ የውድድር ዓመት ቀሪ አምስት ጨዋታዎች እያሉ ተመልሶ ወደ ሻምፒዮን ሺፕ መውረዱን ያረጋገጠ ክለብ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.