ካዛንቺስ አካባቢ የነበሩ የልማት ተነሺዎች በኮሪደር ልማት የተቀየረውን አዲሱን ካዛንቺስ ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ካዛንቺስ አካባቢ የነበሩ የልማት ተነሺዎች ዛሬ ማምሻውን በኮሪደር ልማት የተቀየረውን አዲሱን ካዛንቺስ መጎብኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤበ ገለጹ
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ የልማት ተነሺዎቹ ባዩት የልማት ስራ መደሰታቸውን የገለፁበት መንገድ ደግሞ ለቀጣይ ሥራ አቅም ሆኖናል ብለዋል።
በጋራ መክረን፣ በጋራ ስርተን እዚህ ደርሰናል ያሉት ከንቲባዋ÷ ውብ ሆና እንደ አዲስ የለማችዋም ካዛንቺስ የናንተ ናት፣ አቃቂ/ገላን ጉራም የእናንተ ነው ሲሉ ለነዋሪዎቹ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ውብ ፅዱ ሆኖ መገንባት ለዛሬና ለመጪው ትውልድ ኩራት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ሁሌም ኑ ትዝታችሁን አጣጥሙበት፣ ተዝናኑበት፣ ካዛንቺስ ለትውልዱ ስጦታ፣ ለነዋሪው ደስታ እንዲሆን በጎ ፈቃዳችሁን እና ትብብራችሁ ላልተለየን ለእናንተ በእርግጥ ምስጋናችን የላቀ ነው ሲሉም አክለዋል።