Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ ከ20 በላይ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝቱ፤ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም አቅም በተመለከተ በቱሪዝም ሚንስትር ዴዔታ ስለሺ ግርማ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ጉብኝቱን ቱሪዝም ሚንስቴር ከተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ጋር በመተባበር ማዘጋጀታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ መመዝገቡ ይታወቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.