Fana: At a Speed of Life!

የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ደረጃ ለማሳደግ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በከተሞች የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን ደረጃ እንዲሁም በገጠር የመሠረተ ልማት ሽፋኑን ለማሳደግ ከሀገር በቀል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራቾች ጋር እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት አምራቶች ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው፡፡

የአገልግሎቱ ሥራ አስፈፃሚ ጌቱ ገረመው (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓት በከፊል በሀገር ውስጥ አምራቾች እየቀረቡ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ተቋማቸው ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓት አምራቾች ጋር በቅንጅት እየሠራ እንደሚገኝም አስረድተዋል፡፡

የውጭ ምንዛሪን ለማዳን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና ቴክኖሎጂን ለማሸጋገር የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ግብዓት በሀገር ውስጥ መመረቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቅማቸው ከፍ እንዲል፣ በብዛት እና በጥራት እንዲያመርቱ በመድረኩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አገልግሎቱ ከአምራቾች ግብዓቶችን ለመግዛት ሲያደርግ የነበረውን መመዘኛ ማሻሻሉንም አሳውቀዋል፡፡

በክብረወሰን ኑሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.