Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ናቸው ተባለ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ለኑሮ ምቹ የሚያደርጉ፣ ገጽታዋን የሚቀይሩ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድጉ መሆናቸው ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የማህበራዊ ሴክተር ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡

ጉብኝቱ በከተማዋ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት፣ የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የመልሶ ማልማት ስራዎችን ጨምሮ የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ማዕከልን እና ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።

እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ የሚያደርጉ፣ ገጽታዋን በመቀየር ላይ የሚገኙ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም የልማት ሥራዎቹ  አዲስ አበባ ከተማን የተቀናጀ የመሠረተ ልማት የተሟላላት ከተማ እንድትሆን ያስቻሉና ሀገር ወደ ብልጽግና የምታደርገው ጉዞ ጉልህ ማሳያ ናቸው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በከተማዋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የነገዋ የሴቶች ተሐድሶ ማዕከል፣ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.