Fana: At a Speed of Life!

በበልግ ወቅት ከ345 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዘንድሮው የበልግ ወቅት የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር ከ345 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላን በማጠናከር የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራን በቀጣይነት የምናረጋግጥበት ሊሆን ይገባል ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ለበልግ ተከላ ስኬት የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በሕዝቡ ግንባር ቀደም ተሳትፎ በተከናወነ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት፤ የተራቆቱ ተራሮችን መልሶ በማልማት እና በአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም የክልሉን የደን ሽፋን ማሳደግ እንደተቻለ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በበልጉ ወቅት የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር 14 ሚሊየን 500 ሺህ የፍራፍሬ ችግኞች፣ ከ32 ሚሊየን 92 ሺህ በላይ የቡና ችግኞች እንዲሁም 119 ሚሊየን 203 ሺህ 992 የእንሰት ችግኞች በተደራጀ የሕዝብ ተሳትፎ ይተከላሉ ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.