Fana: At a Speed of Life!

የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደርን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሞሮኮ ሮያል አርሚ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ በሪድ የተመራ የሞሮኮ ሮያል አርሚ ከፍተኛ ልዑክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አሥተዳደር ጉብኝት አድርጓል።

የአሥተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በዚሁ ወቅት፤ የኢትዮጵያን የሳይበር ደኅንነት በማረጋገጥ በኩል ተቋማቸው በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል ልማት እና በአሠራር ሥርዓት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አብራርተዋል፡፡

በቀጣይም የሀገራቱን የሳይበር ደኅንነት በማረጋገጥ ረገድ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን የአሥተዳደሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ልዑኩ በበኩሉ፤ ኢትዮጵያ የሳይበር ደኅንነት እና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ብቁና ዘመናዊ ተቋም መገንባት መቻሏን መመልከቱን ገልጿል፡፡

ጉብኝቱ ኢትዮጵያ እና ሞሮኮ በዲፕሎማሲው መስክ ያላቸውን ወዳጅነት ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ብሎም በሳይበር ደኅንነት መስክም ይሁን በሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ልዑኩ በጉብኝቱ ወቅት፤ የቋሙን ምርትና አገልግሎቶች፣ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል እና ሌሎች ሥራዎችን ተመልክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.