Fana: At a Speed of Life!

በቤጂንግ የኢትዮጵያ ቡና ወጪ ምርት የንግድ ለንግድ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በቤጂንግ የኢትዮጵያ ቡና ወጪ ምርቶች የንግድ ለንግድ የቢዝነስ ውይይት አካሂደዋል፡፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው በዚሁ ወቅት፤ ኢትዮጵያ ጥራት ያለውና የጥሩ ጣዕም ቡና መገኛ እንዲሁም የተለያዩ ባህሪያት ያላቸው የበርካታ የቡና ዝርያዎች መገኛ መሆኗን አስረድተዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ቡና ፍላጎት የቻይና ገበያን ጨምሮ በተለያዩ መዳረሻዎች በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ነው ማለታቸውን የኤምባሲው መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያን ቡና አመራረት እና የጥራት ደረጃ ለማሻሻል የተለያዩ ስራዎች በመንግስት በኩል እየተሰሩ መሆኑን ስለመግለፃቸው የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ300 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ቡና ኤክስፖርት በማድረግ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በ28 የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች እና 24 የተመረጡ የቻይና ቡና ኩባንያዎች መካከል በቡና ግብይት ትስስር መፍጠር የሚያስችል ውጤታማ የቡና ንግድ ለንግድ ውይይት ተካሂዷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.