የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት ጽሁፍ፤ ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮች እንዲሁም በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ላይ ለመጪዎቹ ሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል ብለዋል።