1 ሚሊየን ብር ወደሚያሸልመው የፋና ላምሮት ፍጻሜ እነማን ይደርሳሉ…?
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብርቱ ፉክክር ሲደረግበት የቆየው ተወዳጁ ፋና ላምሮት ምዕራፍ 19 በቀጣዩ ሣምንት ይጠናቀቃል፡፡
በፍጻሜው ዋዜማ ነገ በሚኖረው ጠንካራ ፉክክርም ከአምስቱ ተወዳዳሪዎች አንዱ ይሰናበታል፡፡
እንዲሁም አራቱ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ ሣምንት 1 ሚሊየን ብር ወደ ሚያሸልመው የፍጻሜ ውድድር ያልፋሉ።
በነገው ውድድርም በኤፍሬም ጌታቸው፣ ካሳሁን ዘውዱ፣ ዳግም ተፈራ፣ ዮሴፍ ጉልላት እና ብሩክ ሰለሞን መካከል ብርቱ ፉክክር ይጠበቃል፡፡
እነማን ወደ አምሥተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ያልፋሉ ሚለውም በጉጉት የሚጠበቅ ነው፡፡
ዛየን ባንድ በበኩሉ ከባድ ፉክክር የሚደረግበትን የነገውን የግማሽ ፍጻሜ ውድድር የሚያጅብ ይሆናል፡፡
ተጠባቂው ይህ ውድድር ከቀኑ 6 ሠዓት ጀምሮ፤ በሁለቱም የፋና ቴሌቪዠን ጣቢያዎች፣ በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና በድረ-ገጽ አማራጮች በቀጥታ ለተመልካች ይደርሳል፡፡
አድማጭ ተመልካቾችም በ8222 ያልተገደበ ድምጽ በመላክ አራቱን የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች መወሰን ይችላሉ፡፡
በለምለም ዮሐንስ