ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንና ኢንስቲትዩቱ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድርን (ዶ/ር) ጨምሮ የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡
የሁለቱ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው የትብብር መስኮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በዚሁ ወቅት፥ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለሀገሪቱ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ አንጻር በሚገባው ልክ ትኩረት እንዲያገኝ በተለይም የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ሚዲያው ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በኢንስቲትዩቱ የሚከናወኑ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና ዘርፉን በማገዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡
በቀጣይ በሁለቱ ተቋማት መካከል የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ