Fana: At a Speed of Life!

በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን በተመረተ የህክምና ተኪ ምርት 14 ሚሊየን ዶላር ማዳን ተቻለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካል ልዩ ኢኮኖሚ ዞን በተመረተ የህክምና ተኪ ምርት ከውጭ ለግዥ የሚወጣውን 14 ሚሊየን ዶላር ማዳን መቻሉ ተገለጸ።

በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶሎሳ በዳዳ በልዩ የኢኮኖሚክ ዞን 23 ኩባንያዎች የለማ መሬት እና መሰረተ ልማት እንደቀረበላቸው ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።

ከነዚህም ውስጥ ሁለት ኩባንያዎች ወደ ስራ ገብተው ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረቡ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህም የህክምና መሳሪያዎች ከውጭ ሲገቡ በነበረበት ጊዜ ይወጣ የነበረውን 14 ሚሊየን ዶላር ማዳን ማስቻሉን ጠቁመዋል።

በቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካል ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከአንድ መስኮት አገልግሎት ባሻገር የተለያዩ ማበረታቻዎች መኖራቸውንም አመላክተዋል።

በጸጋዬ ንጉሥ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.