Fana: At a Speed of Life!

ፈጠራ እና ሀብትን በማቀናጀት የወባ ስርጭትን ለመግታት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አዳዲስ ፈጠራ እና ፍጥነት እንዲሁም ሀብትን በማቀናጀት የወባ ስርጭትን ለመግታት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገለጹ።

ዓለም አቀፍ የወባ ቀን ለ18ኛ ጊዜ “አዳዲስ ፈጠራዎችን እና ሀብትን በማቀናጀት በሁሉ አቀፍ ቅንጅት ወባን እንግታ” በሚል መሪ ሐሳብ በጅማ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

የጤና ሚኒስስር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ አዳዲስ ፈጠራ እና ፍጥነት እንዲሀም ሀብትን ማቀናጀት የወባ ስርጭትን ለመግታት እየተሰራ ነው።

የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ነጻነት ወርቅነህ (ፕ/ር) በበኩላቸው÷ በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት በወባ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል።

በክልሉ በበጅት ዓመቱ ስምንት ሚሊየን የወባ መከላከያ አጎበር ተጋላጭ ለወኑ አባባቢዎች መሰራጨቱን እና የወባ ስርጭት 80 በመቶ መቀነስ መቻሉንም ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ የወባ በሽታ ስርጭት በዓለም ደረጃ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱም ተመላክቷል።

በወርቃፈራው ያለው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.