ማንቼስተር ሲቲ ከኖቲንግሀም ፎረስት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ማንቼስተር ሲቲ የውድድር ዓመቱን ያለ ዋንጫ ላለማጠናቀቅ በዋንጫ ፉክክር ውስጥ ለመቆየት ይፋለማል።
ማንቼስተር ሲቲ በሩብ ፍፃሜው ቦርንመዝን በማሸነፍ ለግማሽ ፍፃሜው ሲበቃ ኖቲንግሀም ፎረስት በበኩሉ ብራይተንን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀሉ ይታወሳል።
ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር ካደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስ በርስ ግንኙነቶች ማንቼስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ ኖቲንግሀም ፎረስት በአንዱ ድል አድርጎ በአንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በፍፃሜው ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይፋለማል።