በአማራ ክልል 9ኛው ክልል አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ሥራና ስልጠና ቢሮ ዘጠነኛው ክልል አቀፍ የቴክኖሎጅ፣ የክኅሎት፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ንግድና ትርዒት ኤግዚቪሽን እና የደረጃ ሽግግር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የሥራና ክኅሎት ሚንስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ እና የፌደራል ከፍተኛ መራሮች ተገኝተዋል፡፡
በውድድሩ ላይ የደሴ ከተማ ወይዘሮ ስኅን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በሦስት የክኅሎት እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንደሚወዳደር የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
ሥምንት ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው መቅረባቸውም ተጠቁሟል፡፡
እንዲሁም 24ቱ ደግሞ ከአነስተኛ መብቃት ወደ ታዳጊና መካከለኛ ባለሀብት ሽግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡
በተጨማሪም 12 ያህሉ ደግሞ በክኅሎትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡