በሳዑዲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ3 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 3 ሺህ 240 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
እነዚህ ወገኖች የተመሰሉት በሣምንቱ ውስጥ በተደረጉ 9 ዙር በረራዎች መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ባለው ዜጎችን የመመለስ ሥራ እስከ አሁን 22 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራም እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡