Fana: At a Speed of Life!

በኢራን ወደብ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር 25 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢራን ወደብ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር 25 ሲደርስ 800 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸው ተገልጿል፡፡

ፍንዳታው የደረሰው ቅዳሜ ጧት በደቡባዊ ባንዳር አባስ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ሻሂድ ራጃኢ የንግድ ወደብ ላይ ነው።

በአደጋው በአቅራቢያ ያሉ ሕንፃዎች እና መኪናዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት እና ከተጎዱት በተጨማሪ ስድስት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።

የአየር ላይ ምስሎች ቢያንስ ሶስት አካባቢዎች በእሳት መያዛቸውን እና የኢራን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ከጊዜ በኋላ እሳቱ ከአንድ ኮንቴነር ወደ ሌላ እየተዛመተ መሆኑን አረጋግጠዋል።

አደጋውን ተከትሎ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዛሬ ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን የዓይን እማኞችን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ፍንዳታው ከተከሰተ በኋላ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ተቀጣጣይ ቁሶች ወደሚከማቹበት ኮንቴይነሮች ተዛምቷል።

የኢራን ፕሬዚዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀው፤ ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.