Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሕመድ ሺዴ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

የአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር፤ ኢትዮጵያ እያደረገች በሚገኘው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ኢኮኖሚውን የማዘመን አዎንታዊ ግስጋሴ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በመንግሥት በተወሰዱ የማክሮ ኢኮኖሚ የማሻሻያ እርምጃዎች ምክንያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም አቀፍ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሆኖም ዕድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

አቶ አሕመድ ሺዴ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ያላትን አጋርነት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቀጣናዊ ሰላም እና በሌሎችም ጉዳዮች ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

በተመሳሳይ ከልዑኩ ጋር የመከሩት የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቭ ጃጋዴሳን፤ ተቋማቸው በአይሲቲ፣ ማዕድን፣ መሠረተ ልማት እና ግብርና የኢንቨስትመንት አማራጮች በኢትዮጵያ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አረጋግጠዋል፡፡

አቶ አሕመድ ሺዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗ በመግለጽ፤ የልማት ፋይናንስ ኮርፖሬሽኑ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት እንዲያደርግ ጋብዘዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.