Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች የለንደን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ45ኛው የለንደን ማራቶን በሴቶች ምድብ የፓሪስ ኦሊምፒክ የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡

አትሌት ትግስት ርቀቱን ለመጨረስ 2 ሠዓት ከ15 ደቂቃ ከ50 ሠከንድ ፈጅቶባታል፡፡

በዚሁ ውድድር መርሐ-ግብር ኬንያዊቷ አትሌት ጄፕኮስፔ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ሲፋን ሀሰን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

የለንደን ማራቶን በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲንየም ደረጃ ያለው ከዓለም ትላልቅ ማራቶን ውድድሮች መካከል አንዱ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.