በጃፓን በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ዳዊት ወልዴ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጃፓን ጊፉ ከተማ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ዳዊት ወልዴ አሸንፏል፡፡
ውድድሩን 1፡00፡06 በሆነ ሰዓት በመግባት በአንደኝነት ያጠናቀቀው አትሌት ዳዊት ወልዴ፤ በውድድሩ ሲሳተፍ የመጀመሪያው እንደሆነ ተገልጿል።
በሴቶች በተካሄደው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ጎይተይቶም ገብረስላሴ 1:08:29 በሆነ ሰአት በመግባት በሁለተኝነት ጨርሳለች፡፡
በሲድኒ 2000 የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ እና የጊፉ ተወላጅ ናኦኮ ታካሃሺ የተመሰረተው ይህ ውድድር የአትሌቲክሱን ስፖርት የበለጠ ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል፡፡