የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በድጋሚ ተራዘመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ-ግብር የነበረው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በድጋሚ ተራዝሟል፡፡
በሐዋሳ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ጨዋታው በዕለቱ ሳይደረግ ተራዝሞ የነበረው ጨዋታ ዛሬ ደግሞ 84ኛ ደቂቃ ላይ የስታዲየሙ መብራት ሊበራ ባለመቻሉ ጨዋታው ተቋርጦ በድጋሚ ተራዝሟል፡፡
ጨዋታውን ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሽመክት ጉግሳ እና አሸናፊ ጥሩነህ ግቦች 2 ለ 0 እየመራ ነበር።
የቀሪዎቹ ደቂቃዎች ጨዋታ በውድድር ደንቡ መሠረት ነገ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ጠዋት 3 ሠዓት ከ30 ላይ በሐዋሳ ዩንቨርሲቲ ስቲዲየም የሚካሄድ ይሆናል፡፡