ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባህል፣ ኪነ ጥበብና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በኢትዮጵያ ከሩስያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተረክሂን ጋር በባህል፣ ኪነ ጥበብ እና ስፖርት ዘርፍ በጋራ መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ኢትዮጵያ የብዝሃ ባህል ባለቤት እና ታሪካዊ ሀገር እንደመሆኗ ከሩስያ መንግስት ጋር በዘርፎቹ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑ ተነስቷል።
ኢትዮጵያ ለብሪክስ አባል ሀገራት ባህሏንና እና ኪነ ጥበቧን ለማስተዋወቅ እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር እየሰራች ያለውን ስራ የሩስያ መንግስት በመደገፍ በትብብር እንደሚሰራም ተገልጿል።
በቀጣይ የጋራ የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር በሚያስችሉ ስራዎች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።